አማኑኤል ሆይ መድኃኒቴ ሆይ አትተወኝ አንተ ሞትን እንዳላይ/2/ የግብፅ ከተማ ደምቃ ስትታየኝ ተስሎንቄ አድጋ ለዓይኔ ስትስብኝ ኤልሻዳይ ኢየሱስ ልቤን መልስልኝ/2/ መታመን በሰው ላይ ምንም አይጠቅምም መከታነት በሰው ለእኔ አይሆንም አትተወኝ አንተ አምላክ ዘለዓለም/2/ የሚያጽናናኝ የለም እኔ እንዲህ ስከፋ ህምልምም ሆነብኛል የሰው ሁሉ ተስፋ ቃልህን የሚታጥፈው አንተ ከእኔ አትጥፋ/2/