ዋ ለነፍሴ ምንም ስንቅ አልያዝኩኝ /2/ አዬ ለእኔሰ ወዮልኝ ዋ ለነፍሴ ምንም ስንቅ አልያዝኩ ነፍሴን እየጎዳሁ ሳስብ ስለሥጋ ዓለም ስትሰበኝ እዳላገኝ ዋጋ መንፈስህን ስጠኝ ከበደል እንጻኝ ቃልህን እሰማለሁ ማስተዋል የለኝም ፍጹም ሆኖ መቆም ጌታ ሆይ አቃተኝ ታዲያ እንደፈቀድህ እንዴት ብዬ ልገኝ ድካሜን ታውቃለህ አምላክ ሆይ አበርታኝ አለቅሳለሁ ጌታ ከእግርህ ስር ወድቄ ሕይወቴ ተዛብቶ በኃጢአት ማቅቄ ዘመኔን ጨረስኩኝ መልካምን ሳልሠራ ቸርነትህ ይርዳኝ ልኑር ከአንተ ጋራ ፈተናው ከበደኝ ለነፍሴ ፈራሁኝ ደስታ ከእኔ አርቆ ቢበዛ ሃዘኔ አትተወኝ አንተ ሁንልኝ ከጎኔ