ዓለም ወረተኛ ከዳተኛ ነች/2/ ዛሬ ከአንተ ጋር ናት ነገ ከሌሎች /2/ አምላክ ለመኖሩ እኛ ማሰረጃ ነን/2/ እልፍኝ ያለ ሠሪው በምንም አላየን/3/ አለም ኃላፊ ናት እናስተውል ሰዎች/2/ እንደ ጠዋት ጤዛ እንደጥላችን ነች/3/ አስተውል ወንድሜ በተሰጠህ ተስፋ/2/ ለሥጋህ አድልተህ ነፍስህ እንዳትጠፋ /3/ ሰዎች አንታለል ለሚቀረው ዓለም/2/ እኛስ እናልፋለን ቃሉ ግን አያልፍም /3/ አምላክ የለም ቢሉ የተሳሳቱት/2/ የህልም እሩጫ ነው ከንቱ መዋተት/3/ መራቀቅ ቢበዛ በሆነው ባልሆነው በቁመቱ ስንዝር የሚጨምር ማነው/3/