colormap #003366#336699#3366CC#003399#000099#0000CC#000066#006666#006699#0099CC#0066CC#0033CC#0000FF#3333FF#333399#669999#009999#33CCCC#00CCFF#0099FF#0066FF#3366FF#3333CC#666699#339966#00CC99#00FFCC#00FFFF#33CCFF#3399FF#6699FF#6666FF#6600FF#6600CC#339933#00CC66#00FF99#66FFCC#66FFFF#66CCFF#99CCFF#9999FF#9966FF#9933FF#9900FF#006600#00CC00#00FF00#66FF99#99FFCC#CCFFFF#CCCCFF#CC99FF#CC66FF#CC33FF#CC00FF#9900CC#003300#009933#33CC33#66FF66#99FF99#CCFFCC#FFFFFF#FFCCFF#FF99FF#FF66FF#FF00FF#CC00CC#660066#336600#009900#66FF33#99FF66#CCFF99#FFFFCC#FFCCCC#FF99CC#FF66CC#FF33CC#CC0099#993399#333300#669900#99FF33#CCFF66#FFFF99#FFCC99#FF9999#FF6699#FF3399#CC3399#990099#666633#99CC00#CCFF33#FFFF66#FFCC66#FF9966#FF6666#FF0066#CC6699#993366#999966#CCCC00#FFFF00#FFCC00#FF9933#FF6600#FF5050#CC0066#660033#996633#CC9900#FF9900#CC6600#FF3300#FF0000#CC0000#990033#663300#996600#CC3300#993300#990000#800000#993333

ለውለታህማ

ለውለታህማ ጌታ ምን እንከፍልሃለን ለማይነገር ስጦታህ ተመስገን እንልሃለን/2/ ማቃችንን ቀይረህ አዲስ ላለበስከን ቁስላችንን አጥበህ ዘይት ለቀባኸን ጠላት ሲያዋርደን አንተ ላከበርከን ለዚህ ሁሉ ውለታህ ምን እንከፍልሃለን እኛ በበደልን ትእዛዝህን ጥሰን አንተ በመስቀል ላይ ደምህ ፈሰሰልን ፍቅርህን ስናስብ እጅግ ይድነቀናል ለዚህ ሁሌ ውለታህ ምን ይከፈልሃል የእኛ ፍቅር ስቦህ ከሰማይ ወርደህ ደካማ ሥጋችንን ተዋርደህ አክብረህ እግራችንን አጥብህ ፍቅር ላስተማርከን ውለታህ ከብዶናል ምን እንከፍልሃለን/2/ ባሮች እንዳልነበርን ልጆች አደረከን መቼም ከማያልቀው በረከት አደልከን ዘለአለማዊ ሕይወት ለሰጠኸን ምስጋናችን ይድረስኽጸጋህ አይለየን