የሰው ልጅ በኃይልህ ፈጽሞ አትመካ/2/ አንድ አምላክ አለና በኃይሉ ኃይልን የሚለካ/2/ አዝ --- ኃይል አንደ ሶምሶን ከአምላክ ሲሰጥ እንጃ/2/ በጉልበት መመካት ለማንም አይበከጂ/2/ ሰናክሬም ቢነሳ በሕዝቅያስ ላይ/2/ የደረሰበትን አልሰማህም ወይ/2/ አዝ --- ጎልያድ በኃይሉ ዳዊትን ቢንቀው/2/ አዋረደው እንጂ ኃይሉ ምን ጠቀመው /2/ እንደ ዳታንና እንደአቤሮን አይሆንም በግድ/2/ ተመርጦ ነው እንጂ ለክብር በአምላክ ፈቃድ/2/ ክህነትን ለአሮን ሕግንም ለሙሴ/4/ ከሰው ሁሉ መርጠው ሰጧቸው ሥላሴ