የሰማዩ አባት ደግ ነህ መልካም እረኛ ነህ ለሁሉም ጊዜ አለህ በጊዜው ሁሉን ታደርጋለህ/2/ አዝ --- ማን ያበድርሃል እግዚአብሔር ለአንተ ብድራትን ሁሉን ታደርግለህ በኃይልህ ችሎታህ አንችልም እግዚአብሔር እኛ በአንተ ፊት አዝ --- ከታናሽነቴ ጀምረህ እኔን ያስተማርከኝ የቃልህን ወተት በቤትህ ለእኔ የመገብከኝ ለአንተ የምከፍልህ አግዚአብሔር አንዳችም የለኝ አዝ --- ለማልቀስ ጊዜ አለው አምላኬ ደርሶ ለመሳቅ ከራሣችን ፀጉር አንዲቷን ጥቂቱን ሣናውቅ የእኛስ ተግባር ሆኗል ለሁሉም ደርሶ መጨነቅ/2/