colormap #003366#336699#3366CC#003399#000099#0000CC#000066#006666#006699#0099CC#0066CC#0033CC#0000FF#3333FF#333399#669999#009999#33CCCC#00CCFF#0099FF#0066FF#3366FF#3333CC#666699#339966#00CC99#00FFCC#00FFFF#33CCFF#3399FF#6699FF#6666FF#6600FF#6600CC#339933#00CC66#00FF99#66FFCC#66FFFF#66CCFF#99CCFF#9999FF#9966FF#9933FF#9900FF#006600#00CC00#00FF00#66FF99#99FFCC#CCFFFF#CCCCFF#CC99FF#CC66FF#CC33FF#CC00FF#9900CC#003300#009933#33CC33#66FF66#99FF99#CCFFCC#FFFFFF#FFCCFF#FF99FF#FF66FF#FF00FF#CC00CC#660066#336600#009900#66FF33#99FF66#CCFF99#FFFFCC#FFCCCC#FF99CC#FF66CC#FF33CC#CC0099#993399#333300#669900#99FF33#CCFF66#FFFF99#FFCC99#FF9999#FF6699#FF3399#CC3399#990099#666633#99CC00#CCFF33#FFFF66#FFCC66#FF9966#FF6666#FF0066#CC6699#993366#999966#CCCC00#FFFF00#FFCC00#FF9933#FF6600#FF5050#CC0066#660033#996633#CC9900#FF9900#CC6600#FF3300#FF0000#CC0000#990033#663300#996600#CC3300#993300#990000#800000#993333

አቤቱ ልንበርከክ

አቤቱ! ልንበርከክ ልማር ልቤን አስተምረኝ ወድቄ እንዳልቀር አቤቱ! ለመማር ስፈልግ ደጅህን ስጠና ተመለስ ይለኛል የሥጋ ፈተና አቤቱ! በልቤ እርሻ ላይ የዘራኸውን ቃል ዲያብሎስ ወፍ ሆኖ ከልቤ ይለቅማል አቤቱ! ልንበርከክ ልማር ልቤን አስተምረኝ ወድቄ እንዳልቀር አቤቱ! ይህንንም ያንም ሁሉን ነገር ስመኝ ከቤትህ እንዳልርቅ ቃልህ ይመልሰኝ አቤቱ! አባት ለአንድ ልጁ እንደሚራራለት በሞት አትቅጠፈኝ በደሌን በማየት አቤቱ ልንበርከክ ልማር ልቤን አስተምረኝ ወድቄ እንዳልቀር አቤቱ! ውለታ ምን ይሆን ጌታ የአንተ ፍቅር ምን ይከፈለዋል ሲያጠፋ ለሚምር አቤቱ! ቁስሌን አጠብክልኝ አደረከኝ ሰላም ተአምርህን ዘርዝሬ እኔም አልዘልቀውም አቤቱ! ልንበርከክ ልማር ልቤን አስተምረኝ ወድቄ እንዳልቀር አቤቱ! ኃያል ነህ ገናና አማካሪም የለህ ፍርድህ ሚዛናዊ የእውነት አባት ነህ አቤቱ! የተዋረደውን አንተ ታከብራለህ መልክና ቁመና መች ትመዝናለህ