ላይቀር መሞት አፈር መልበስ መግባት ከመቃብር መስሎኝ ቋሚ ይህ ሥጋዬ ለእርሱ ብቻ ስጥር ዘመን መቁጠር እለት ወራት ክረምት በጋ ሌሊትና ቀን ሲፈራረቅ ሲጨልም ሲነጋ በማየቴ ሆነ መደሰቴ/2/ ኽረ ወዲያ ወዲልኝ ዋይ ብለሽ ለነፍሴ አድርጎኛል የኃጢአት ምንጭ ደካማው መንፈስ መሐሪ አምላክ ለጋሰ ጌታ ቸሩ ፈጣሪዬ አንተ እኮ ነህ ለዘላለም ለእኔ መመኪያዬ ይቅር በለኝ ምሕረትህ አይራቀኝ/2/