በኢያሪኮ መንገድ ጌታ አንተ ስታልፍ ግፊያ ሆኖ ስደነቃቀፍ የዳዊት ልጅ ማረኝ ብዬ ተማጸንኩህ ዓይኔንም ፈወስከኝ ዛሬ ማየት ቻልኩኝ/2/ አንተን እንዳላይ ቁመቴ አጠረብኝ ከፊት እየሮጥኩ ከዛፍ ላይ ወጣሁኝ ጌታ ሆይ ጠረኸኝ ዘኬዎስ ሆይ አልከኝ ቤቴ እንድትገባ ፍቃድህ ሆነልኝ/2/ ሐሴትም ሆነልኝ በጣምም ደስ አለኝ አንተን በእንግድነት በቤቴ ተቀበልኩኝ ኃጢአቴን ሁሉ በአንተ ፊት ጥያለሁ ሀብቴን አካፍል ዘንድ እንዲገባ አውቃለሁ/2/ የክፋትን ገንዘብ መስብሰቤን ትቼ አንተን ልክተልህ ሁሉን ረስቼ ኑሮዬንም ባርከው የሕይወት ዘመኔን መርጫለሁ አንተን በቤትህ መኖሬን/2/