colormap #003366#336699#3366CC#003399#000099#0000CC#000066#006666#006699#0099CC#0066CC#0033CC#0000FF#3333FF#333399#669999#009999#33CCCC#00CCFF#0099FF#0066FF#3366FF#3333CC#666699#339966#00CC99#00FFCC#00FFFF#33CCFF#3399FF#6699FF#6666FF#6600FF#6600CC#339933#00CC66#00FF99#66FFCC#66FFFF#66CCFF#99CCFF#9999FF#9966FF#9933FF#9900FF#006600#00CC00#00FF00#66FF99#99FFCC#CCFFFF#CCCCFF#CC99FF#CC66FF#CC33FF#CC00FF#9900CC#003300#009933#33CC33#66FF66#99FF99#CCFFCC#FFFFFF#FFCCFF#FF99FF#FF66FF#FF00FF#CC00CC#660066#336600#009900#66FF33#99FF66#CCFF99#FFFFCC#FFCCCC#FF99CC#FF66CC#FF33CC#CC0099#993399#333300#669900#99FF33#CCFF66#FFFF99#FFCC99#FF9999#FF6699#FF3399#CC3399#990099#666633#99CC00#CCFF33#FFFF66#FFCC66#FF9966#FF6666#FF0066#CC6699#993366#999966#CCCC00#FFFF00#FFCC00#FF9933#FF6600#FF5050#CC0066#660033#996633#CC9900#FF9900#CC6600#FF3300#FF0000#CC0000#990033#663300#996600#CC3300#993300#990000#800000#993333

ማረን አባታችን

ማረን አባታችን ማረን ማረን እግዚአብሔር ከዘመኑ መቅሰፍት ከልለህ አውጣን ሰውረህ እግዚአብሔር ሆይ ይብዛ ምሕረትህ ሕፃናት ሲያለቅሱ እናት አባት አጥተው ተስፋቸው ሲጨልም አዛውንት ጧሪ አተው አትጨክን አምላክ ቁጣህን መልሰው የዘመኑን ንዳድ እሳቱን አብርደው አዝ --- ያለ እድሜው ሲቀጠፍ ወጣሩ አንደ አበባ ወላጅ አንጀቱ ሲያር ሲታጠብ በእንባ እዘንልን አምላክ ምሕረትህን አብዛ ከመድኃኒት አንተ ነህ ለሕይወተችን ቤዛ አዝ --- እንኳን የታመመው የቆመው ሲሰጋ የሥጋዊ ጥበብ መላም አጥቷል ዋጋ ከሰው ወገን የለም አንዳች ቅንጣት ተስፋ ምሕረትህ ይብዛልን በሞት እንዳንጠፋ አዝ --- ሕግህ ከለላ ነው ከጥፋት መዳኛ አንድ ለአንድ እንጽና እንዳናዝን እኛ ሌላ መላም የለ ቃልህ ያድነኛል ከዘመኑ ስጋት ነጻ ያወጣናል