ልመናዬን ስማኝ ቃሌን አድምጠኝ/2/ እውነተኛ አምላክ ሰላምህን ስጠኝ/2/ ክርስቲያኖች ሁሉ ትእዛዙን አክብሩ ምስጋናን አቅርቡ ስገዱ ዘምሩ የጌታን አመጣጥ ለዓለም ንገሩ ደቀመዛሙርቱ ወንጌል አስተምሩ አዝ --- በመልካም የሚሄድ ጽድቅን የሚሰራ የፈጣሪውን ስም በከንቱ የማይጠራ ይጎበኛል በምድር ከሰማዩ ስፍራ በቀኝ ይቀመጣል ከቅዱሳን ጋራ አዝ --- ስለጠላቶቼ በጽድቅ ምራኝ በጦር ቃል ከበቡኝ ተሳለቁብኝ መሐሪ ይቅር ባይ መጠጊያ ሁነኝ አንተ በቸርነትህ ይቅርታ ስጠኝ