ሰው ለሰው /2/ ቢፋቀር ምነው /2/ ለሰው ይመስለዋል ብዙ የሚቆይ ግን በድንገት ያልፋል ሁሉንም/2/ ሳያይ ሀብትን ከማቻል ቀኑን ሳውቀው በድንገት ይጠራል/2/ አይከተለውም የሰው ልጅ በተራ መጠራቱ ላይቀር ምነው አንዱ ለአንዱ መቃብር/2/ ባይቆፍር አይጠቅምም መጨነቅ እንዲያው ለውበት ይረግፋል ይጠፋል ሁሉም/2/ ከመሬት ዋ ቁንጅና ከንቱ ማማርም ብላሽ አፈር ትቢያ ሲሆን ሲጨለም/2/ሲመሽ ደሀ ባለጸጋ አንድ ነው መንገዱ በጨርቅ ተገንዞ በሳጥን/2/ መሄዱ ሰው ዙሪያውን ቢያጥር መዝጊውን ቢሠራ በሕንፃ ላይ ሕንፃ ቢያስመስል ተራራ አይቀርም መሄዱ ሁሉም/2/ በየተራ