መጽሐፍቅዱስን ሁሉም ያነበዋል ምእራፍና ቁጥሩን ሁሉም ይጠቅሰዋል በዚህ ብቻ አይበቃም ተርጓሚ ያሻዋል/2/ እንደፈቃዳችን ብንተረጉመው/2/ በውጥን የሚልቀው ስህተቱ ብዙ ነው/2/ ከቶ በሰው ፈቃድ ትንቢት እንዳልመጣ /2/ ይነግረናል መጽሐፍ ከሕግ እንዳንወጣ ይመክረናል መጽሐፍ ከሕግ እንዳንወጣ እንጠይቅ መምህራን ያሉት በደረጃ /2/ እናንብብ መጽሐፍት ይሁኑን ማስረጃ/2/