ኑ እንቅረብ መጠራት ሳይመጣ/2/ ሥጋውን እንብላ /2/ ደሙንም እንጠጣ የቀራንዮ በግ የአምላክ ሥጋው ተሰውቶልናል እንመገበው እድፉን ኃጢአታችን በንስሓ አንጽተን እንቀበልው አምነን በልጅነታችን አዝ --- መቅረብ ወደጌታ በእውነት የሚገባው በስተርጅና አይደለም በወጣትነት ነው ጨረቃና ፀሐይ ደም የለበሱት ከዋክብት በሰማይ የተነጠፉት ይኸው ተፈተተ እሳተ መለኮት/2/ አዝ --- ቅድስት እናታችን ቤተክርስቲያን ትመግበናለች ሥጋና ደሙን የአማኑኤል ሥጋ ይኸው ተዘጋጀ ለግብዣ ተጠራን አዋጁ ታወጀ አዝ --- መጥቁ ተወለደ እንቅረብ በእልልታ በኋላ አይረባም ዋይታና ጫጫታ ይህንን እድል ፈጥነን እንጠቀምበት ዓለምን አልያዝንም ብዙ ልንቆይበት አዝ --- አሁኑ ቅረቡ ታውጇል አዋጁ የይለፍ ደብዳቤ ስንቅን አዘጋጁ ይህ ዓለም ጠፊ ነው በሀብት አትመኩ ብሏል አምላካችን ተስፋችሁን እንኩ