ነፍሴ ሆይ እግዚአብሔርን በቅን አገልግይ/2/ የተቀበለው በቀራንዮ ያን ሁሉ መከራ በመስቀሉ ላይ ለአንቺ ሲል ነውና ነፍሴ ሆይ ተዘጋጅተሸ ኑሪ ሁልጊዜ በነገ በዛሬ እንዳትታለዪ/2/ ነፍሴ ሆይ በንስሓ ጥምቀት ታጠቢና ክቡር ደሙን ጠጪ ሥጋውንም ብይ/2/ ነፍሴ ሆይ ዘላለም በደስታ እንድትኖሪ ከዘላለም ቤትሽ መንግሥተ ሰማይ/2/ ነፍሴ ሆይ