ወደአንተ እሰግዳለሁ ሳለሁ በሕይወቴ ለአንተም እገዛለሁ እስከ እለተ ሞቴ አንተ ነህና መድኃኒቴ የዘላለም ቤቴ /2/ የነፍስ የሥጋዬ የሕይወቴ ቤዛ አትበለኝ ችላ በደሌ ቢበዛ አንተን አምኜ እኖራለሁ ወዴት እደርሳለሁ አንተን አምኜ እኖራለሁ በአንተም እመካለሁ ሳይመሽብኝ ቀኑ ሳይጨልም ድንገት በጽድቅ ጎዳና ልጓዝ ወደፊት ምራኝ መንገዱን አሳየኝ እንዳልሳሳት(፪)