አንድ ጊዜ የእግዚአብሔር ሆኛለሁ/2/ በፍቅሩ ተስቤ በደሙ ድኛለሁ ዓለም ተይኝ ንቄ ትቼሻለሁ ጥበበኛው ሰይጣን በመጣው ቢመጣ ዳግም ተመልሼ ከእቅፍህ ላልወጣ በመስቀሉ ግርጌ አርፌ እኖራለሁ ዓለም ተይኝ የእግዚአብሔር ሆኛለው አዝ --- ቢያሙኝ ቢያጥላሉኝ ቢሳለቁብኝ ውርደትን ተንኮልን ቢሸርቡብኝ ለእኔ እንደው ደስታ ነው ሐዘንም የለኝ ሰይጣን እፈር የክርስቶስ ነኝ አዝ --- ጓደኞቼ ጠሉኝ ተለውጬባቸው የጥንቱን ፀባዬን ስለነፈግኹአቸው ብቻዬን የሆንኩኝ ቢመስለኝም ለእኔ ጌታ እንደሆን አለልኝ ከጎኔ አዝ ---