መቼ ነው ጌታ ኧረ መቼ ነው መቼ ነው ጌታዬ እንደቃልህ የሚሆን ጉዞዬ/፪/ አልተማርኩም አልል አስተምረኸኛል/2/ ቃለህን እንደ ወተት አጠጥተኸኛል/2/ መቼ ነው ጌታ ኧረ መቼ ነው መቼ ነው ጌታዬ እንደቃልህ የሚሆን ጉዞዬ/፪/ የታል አኗኗሬ አንተን የሚመስለው/2/ በልማድ ሕይወት ነው የምመላለሰው/2/ መቼ ነው ጌታ ኧረ መቼ ነው መቼ ነው ጌታዬ እንደቃልህ የሚሆን ጉዞዬ/፪/ ይህ አንደበቴማ በቃልህ ሠልጥኗል/2/ ልቦናዬ ካንተ ከፊትህ ኮብልሏል/2/ መቼ ነው ጌታ ኧረ መቼ ነው መቼ ነው ጌታዬ እንደቃልህ የሚሆን ጉዞዬ/፪/ አንተን እንደማውቅህ አብዝቼ ባወራ/2/ የተዘራው ሁሉ ፍሬ አላፈራ/2/ መቼ ነው ጌታ ኧረ መቼ ነው መቼ ነው ጌታዬ እንደቃልህ የሚሆን ጉዞዬ/፪/ እዘንልኝና መንገዴን አቅናልኝ/፪/ የአመጻ ሥራዬን በደሌን ተውልኝ/2/ መቼ ነው ጌታ ኧረ መቼ ነው መቼ ነው ጌታዬ እንደቃልህ የሚሆን ጉዞዬ/፪/ ቃልህ እንዳይሰደብ በእኔ ድካም(2) አርመው እርሻህን መድኃኔዓለም(2) መቼ ነው ጌታ ኧረ መቼ ነው መቼ ነው ጌታዬ እንደቃልህ የሚሆን ጉዞዬ/፪/ ከእስራቴ አውጥተህ ነፃነት ስጠኝ(2) በቀኝህ አቁመህ ጌታዬ ሆይ ባርከኝ(2) መቼ ነው ጌታ ኧረ መቼ ነው መቼ ነው ጌታዬ እንደቃልህ የሚሆን ጉዞዬ/፪/ ኃጢያት ሞትን ወልዶ እንዳያጠፋኝ(2) የብርሃን ፊትህ ይገለጽልኝ(፪)