እስከ መቼ ነው የማልለወጠው ባልተሰበረ ልብ የምመላለሰው/2/ በሰጠኸኝ ጸጋ ድካሜ ተከድኖ ዓለም ይክበኛል አልቆና አግኖ ይህን ከንቱ ወጥመድ ጣለው ከኋላዬ ትንሽ ሰው መሆኔን ይወቅ ህሊናዬ /2/ አዝ --- ፀሐይ ስትቀላ ከዋክብት ሲረግፉ ለገናናው ክብርህ ወድቀው ሲሸነፉ ለሁለት ሲከፈል ድንጋያማው አለት የእኔ ልብ መቼ ይሆን የሚሸነፍለት/2/ ቃልህን ስስማ ልቤን ይነካኛል ጽታቅን አስባለሁ ሐዘን ይሰማኛል ወዲያው ተመልሼ ሁሉን እረሳለሁ ለዚህ ዓለም ስብከት ልቤን እከፍታለሁ/2/