ከወገኔ ጋራ እዘምራለሁኝ በደስታ በሐሴት ስሙን እጠራለሁኝ ምግብና መጠጤ አምላኬ ነውና ዘወትር አቀርባለሁ ለጌታ ምስጋና/2/ አዝ --- ሕዝቡ ተስብስቦ በቤተ ክርስቲያን ሲዘምር ደስ ይላል በአንድነት ሆነን በረከት የሞላው ዝማሬ ይገርማል ከዕጣኑ ጋር ወደ ላይ ይወጣል/2/ አዝ --- ቀሳውስቱ ሌሊት ማኅሌት ሲያቀርቡ ከመላእክት ጋራ ወረብ ሲወርቡ ብርሃን ለብሰን በደሰታ ስንዘምር ትዝታው ልዬ ነው ኅሊና ሲሠውር አዝ --- ራእይ ነውና ኑና ተመልከቱ ሰዎች ሲዘምሩ እንደመላእክቱ የጽጌው ዝማሬ የትንሣኤው ደስታ ልዩ ዝማሬ ነው እዳንዳይመስለን ተርታ አዝ ---