እያለፈ ነው ዘመኔ ትእዛዙን ሳልፈጽም ወየው ለእኔ/2/ በጠራኝ ጊዜ ምን እላለሁ ና ብሎ ወደእኔ/2/ በጠራኝ ጊዜ ምን እላለው ነይ ብሎ ወደ እኔ በወጣትነቴ ሳልሠራ እያየሁ አለፈኝ ብዙ አዝመራ/2/ ከእንግዲህ በመሥራት ጌታ ሆይ ልኑር ከአንተ ጋራ/2/ የማስብበት በየለእቱ ንጹሕ ልብን ስጠኝ አቤቱ /2/ ከትእዛዝህ ወጪ በመሆን እዳልቀር በከንቱ /2/ እንደየሥራው ለመስጠት በግርማ መንግሥቱ ሲመጣ/2/ ማን ይሆን የሚቆም ከፊቱ ፊተናን የወጣ/2/ እንዳያስቷችሁ ተጠንቀቁ እየተማራችሁ ከቃሉ/2/ ይመጣሉና በእርሱ ስም አምላክ ነን የሚሉ/2/ ትእግሥትን በመያዝ ሁላችሁ እስከመጨረሻው ጠንክሩ/2/ ያን ጊዜ ይሆናል በእርሱ ዘንድ የማዳን ተግባሩ/2/