እግዚአብሔር መልካም ነው በመከራ ቀንም መሸሸጊያ ነው/2/ ከገነት ሲሰደድ አዳም አባታችን ሞት ነግሶብን ሳለ በእኛ በሁላችን ቃል እንደገባለት ተወልዶ ሊያድነው በመከራ ጊዜ መሸሸጊያ ሆነው/2/ አዝ --- አብርሃም ከካራን ከእናት ከአባቱ ቤት ከነአን ሲገባ ሲሰደድ በእምነት ከተሰጠው ተስፋ አንዳች ሳይጎልበት እንደ ምድር አሸዋ ዘሩን አበዛለት/2/ አዝ --- በሐዘን በችግር በመከራ ጊዜ ጭንቀቴን የሚያርቅ ነው የፍሴን ትካዜ የቀደመው እባብ ሰላሜን ሲነሳኝ እግዚአብሔር መልካም ነው ሐዘኔን አስረሳኝ የቀደመው እባብ ሰላሜን ቢነሳኝ ክርስቶስ ኢየሱስ ሐዘኔን አስረሳኝ