ነብዩ ደንኤል በጾም ስላመነ /2/ ከአንበሶች ጉድጓድ ሕይወቱን አዳነ2/ ኤልያስ የወጣው በእሳት ሰረገላ/2/ በጾም በጸሎት ነው አይደለም በሌላ/2/ የነፍስንም ቁስል ጾም ታድናለች/2/ የሥጋን ፍላጎት እያደከመች/2/ እስቲ ልብ እናድርግ እናስተውል ደግሞ /2/ ጌታ ለሐዋርያት ያላቸውን ቀድሞ/2/ ይህ ርኩስ መንፈስ ሊወጣ የሚችል/2/ በጾም በጸሎት ነው እንደ ወንጌሉ ቃል/2/