የነፍሳችን ቤዛ የቅዱሳን ሀብት/2/ ጸጋን የሚያሰጠን ጾም ነው መድኃኒት/2/ የእስራኤል ልጆች በሙሴ ሲመሩ/2/ በጾም በጸሎት ነው ባሕር የተሻገሩ/2/ ቅዱሳን አባቶች ጾም ነው ጋሻቸው /2/› ወደሕይወት መንገድ የሚመራቸው/2/ ክፍላችን እንዲሆን ከቅዱሳን ጋራ/2/ ፍቅር ቤታችንን በጸሎት እንሥራ /2/ ልባችንም ይሁን የጸሎት ጎዳና/2/ የእግዚአብሔርን መንግሥት እንድንወርስ በጤና/2/