አሐዱስ ሶበ እም ማርያም ተወልደ/2/ ኮነነ ዘመደ/2/ ኮነነ ዘመደ/2/ በአምላክ ኅሊና የታሰበች ከዓለም በፊት የታወቀች በእርሷ ለማደር ቃል ተላከ በነቢያትም ተሰበከ አዝ------------ ከፍጥረቱ አስበልጦ ከሴቶች ሁሉ እርሷን መርጦ ዙፋኑን ትቶ መጣ ወረደ ሥጋዋን ለብሶ ተዋሐደ አዝ------------ በተዋህዶ አከበረን ከእኛ ተወልዶ ዘመድ ሆነን በማህፀኗ ለማደሩ የገጠመ ነው ያ ምስጢሩ