እኔስ በምግባሬ ደካማ ሆኛለሁ እዘኝልኝ ድንግል እለምንሻለሁ /፪/ ያንን የእሳት ባሕር እንዳላይ አደራ ድረሽልኝ ድንግል ስምሽን ስጠራ /፪/ የዳዊት መሰንቆ የኤልያስ መና የናሆም መጽኃኒት ነይ በደመና/፪/ አንቺ ነሽ ጉልበቴ በደከመኝ ጊዜ የልቤ መጽናኛ ረዳት ምርኩዜ /፪/ አፈሳለሁ እንባ በጣም ተጨንቄ እማጸንሻለሁ በደሌን አውቄ/2/