ከፈጣሪ በ ች ከፍጡራን በላይ/2/ ማን አለ እንዳንቺ ድንግል ንፁህ በአለም ላይ /2/ ኦ ድንግል ማርያም ዘላለም/2/ መኩሪያ ነሽ መመኪያ አምላክ ለማደሪያ መርጦ ያዘጋጀሽ/2/ ጽዮን የተባለች ሀገር ድንግል ሆይ አንቺው ነሽ/2/ በሐሳብሽ ድንግል ድንግል በስጋሽ/2/ ከፍጥረ ት ሁሉ ላንቺ ምሣሌም የለሽ/2/ ፍቅሩ ለዘላለም የማይጠገበው/2/ ከስም ሁሉ በላይ ጣፋጭ ድንግል የአንቺ ስም ነው/2/ በእዝራ መሰንቆ በዳዊት በገና/2/ ይገባሻል ላንቺ ድንግል ሁልጊዜ ምስጋና አዝ- - - - - እስኪ ልያዝና ደጋፊ ምርኩዜን እስኪ ልያዝና የረሃብ መድኃኒቴን ወደ አምላኬ ቤት ልሄድ ልቀጥል ጉካዬን/2/ አዝ - - - - - - ለፍርድ ስጠራ በደለኛው እኔ/2/ የእኔ መማጸኛ ድንግል ቁሚልኝ ከጎኔ/2/