አድኝኝ እናቴ ከሥጋ ፈተና ሥጋዬ ከኃጠአት ከቶ አልራቀምና ሸክሜ የከበደኝ ብቸኛ ሆኛለሁ አትለይኝ ድንግል አደራ እልሻለሁ/2/ አዝ...... የአማኑኤል እናት የተዋሕዶ አክሊል አትጥፊ ከመሀል እንድትሆኝን ኃይል ምንም ቢበዛብሽ የእኛ ጉስቁልና ከእኛ ጋር ከሆንሽ አለን ቅድስና/2/ አዝ....... ተስፋዬ ነሽና እመኝብሻለሁ ግራ ቀኝም አልል ምርኮኛሽ ሆኛለሁ ስቅበዘበዝ አይቶኝ ተስፋ የሰጠኝ እግዚአብሔር ይመስገን ኝንቺ ያስጠጋኝ/2/ አዝ...... በሥጋ ደክሜ በነፍስ እንዳልጠፋ እማጸንሻለሁ ድንግል የእኔ ተስፋ የመንግሥቱ ወራሽ እንድሆን አድርጊኝ መልኝም ሥራ መሥራት እኔን አስተምሪኝ/2/ አዝ...... አንቺ የሌለሽበት ጉባኤው ባዶ ነው በቁም የደረቀ ሕይወት የተለየው በመካከል ገብተሽ ሙዪው የገአደለውን ሠርጉ ተደግሷል ገአብኝልን ጓዳውን/2/