ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ድንግል ማርያም/2/ ንጽሕተ ንጹሐን ማርያም ድንግል ማርያም /2/ ማልዳለች ከልጇ ከመድኃኔዓለም /2/ ማልዳለች ከልጇ /2/ ከመድኃኔዓለም ማልዳለች/4/ ልጄ ሆይ ይቅር በል እያለች አባቶቻችን ነቢያት ወሐዋርያት/2/ ጻድቃን ወሰማዕ ት ያማልዳሉ በእውነት ያማልዳሉ /2/ የማልዳሉ በእውነት /2/ ያማልዳሉ ያማልዳሉ /4/ አምላክ ሆይ ይቅር በል እያሉ ሰባቱ ሊቃነ መላእክት ሚካኤል ወገብርኤል ሩፋኤልና ፋኑኤል ሠራዊቶቻቸውም ሁሉ ሰባቱ ሊቃናት መላዕክት አፍኒን ራጉኤልና ሳቁኤል ሠራዊቶቻቸውም ሁሉ ያማልዳሉ ከክፉም ይጠብቃሉ /2/ ያማልዳሉ ከክፉም /2/ ይጠብቃሉ ያማልዳሉ /4/ ከክፉም ይጠብቃሉ በዱር በገደል በበረሀ በዋሻም ያሉ /2/ ያማልዳሉ በእውነት ያማልዳሉ /2/ ያማልዳሉ በእውነት /2/ ያማልዳሉ ያማልዳሉ /4/ አምላክ ሆይ ይቅር በል እያሉ