ኃጢአቴ በዛ እመቤቴ ምሕረት ላኪልኝ ለሕይወቴ የፈጣሪ እናት አዛኝት በአንቺ ነው ማግኘት የጽድቅ ሕይወት/2/ ከሲሑል አውጪኝ አዛኝት የጻድቃን እናት እመቤት ሰላማዊት ናት ሀገረ እግዚአብሔር በአንቺ ነው መወጣት ከኃጢአት ቀንበር/2/ የሚሰግዱልሸ ጻድቃን ሰማዕ ት የሚላኩልሽ ቅዱሳን መላዕክት ከእነርሱ ጋር ነይ እመቤቴ እንዲ ረቀኝ ሰማያዊው አባቴ/2/ አስ ርቂኝ እኔን ከልጅሽ እማልዳለው ከፊትሸ ስምሽን ጠርቶ ያፈረ ማነው የአዳም ተሰፋ ስራሽ ድንቅ ነው/2/ የፍቅር እናት እመቤ ችን አስ ርቂን እኛን ከጌ ችን ዘወትር ነይልን እናቴ ማርያም ላንቺ ቅርብ ነው መድኃኔዓለም