እንደተቆጣኝ አልቀረም በርኅራኄ@ው ማረኝ ቁጣውን መልሶ ለነፍሴ ለልቤ መጽናኛ ሰጠኝ ምን ልክፈለው ለአምላክ ለወደደኝ ልስገድለት ላመስግነው ኃይል ይስጠኝ/2/ ዳገት ቁልቁለት በዛብኝ ለጽድቅ ወደአንተ ስጓዝ ጠላት ተጠምጥሞ ከአንገቴ ጎንጎኔን ነደፈኝ በመርዝ መፍትሔው< ጠፋብኝ ስቃይ በዛብኝ አምላኬ ሆይ በጥበብህ አላቀኝ /2/ ብቻኛ ነኝ ጭንቅ የያዘኝ የጠበበኝ የዓለም ነፋስ ማእበሉ ያንገላ ኝ መላም የለኝ እኔ ተክዤ ቆሜአለሁ ኃይሌ ጉልበቴ መድኃኒቴ በለኝ አለሁ/2/ ቆሜ ሳየው ፊት ኀእላዬን ቀኝ ግራዬን ረዳት የለኝ ምርኩዝ የለኝ ነኝ ብቻዬን የውስጥ የውጭውን ዘርዝሬ የምነግረው እንደነፍሴ የምቆጥረው የማዋየው/2/ አይተህ ይህን መጨነቄን መገፋቴን ላክልኝ ለኔ ድንግልን እመቤቴን ቅዱሳን ሰማእ ት ጻድቃን መላዕክትን ፍጥረትህ ነኝ እንዳልጠፋ አትጨከን /2/ የነበርክ ያለክ ለዘለዓለም የምትኖር ከሥራዬ ባሳዝንህ ዘወትር ያለረዳት አጽናኝ ብቻዬን ያልተውከኝ ተስፋ አልቆርጥም ላመሰግንህ ፍቀድልኝ/2/