ቤዛ የሆነልኝ ስለእኔ የሞተው በፍቅሩ ማረከኝ ጠራኝ በይቅር ው ሰ−ች ሲጸየፉኝ ሊወግሩኝ ሲያስቡ እርሱ ተቀበለኝ በሚራራ ልቡ ቀረብኩኝ ወደ እርሱ ሸክሜን ተሸክሜ ጭነቴ ተራግፎ እንዲቀየር ስሜ ከእግሩ ሥር ተደፋሁኝ አምኜ በደሌን በዕንባዬ አጠብኩት ንጽሕ ቅዱስ ኃጢአተኛ ሳለሁ እርሱ ግን ወደደኝ ሰው ቢፈርድብኝ አምላኬ ነጻ አወጣኝ እንደሰው ፍርድማ ተወግሬ ነበር እርሱ ግን ደገኝ አነጻኝ በፍቅር ሽቱውን ቀባሁት ሰጠሁት መባዬን እርሱም ተቀበለኝ ለወጠው ሪኬን የኃጢአት ኑሮ ጨለማ ሕይወቴን ብርሃን ሆነልኝ ቃሉን በመስማቴ እንደሰው አይደለም ጥፋቴን አይወድም ይምረኛል እንጂ በሰው ላይ አይፈርድም እኔን ከፍ ያደረከኝ ከወዳቂነቴ ምስጋና ይድረስህ የሰማዩ አባቴ