ከዳዊት አብራክ ዘርን ባያስቀርልን ኑሮ አዳም በሲዖል በቀረ በውርደት አንገቱን ቀብሮ ዝም በወረረን በወደቅን ማቅለብሰን ቸርነቱ በዝቶ ግን እመቤ ችንን ሰጠን ፀሐይ ክርስቶስ ወጣ ከቤተልሔም ሀገር የእንጀራ ቤት ነችና የእኛ የፍቅር ባሕር ተበልቶ አይጠግብም የማኅፀንሽ ፍሬ ሕይወት ሆኖን በላነው የማኅፀንሽን ፍሬ ግርማዋ የሚያስፈራ የሙሴ ቤተመቅደስ ተገናኙብሽ በሰላም ሰውና ሥሉስ ቅዱስ የወርቅ መንበር ነሽና ደመና የከበበሽ የሥላሴ ሙሽራ ዕፁብ/2/ ድንቅ ነሽ