ስሜ ተለውጦ ዘማዊ ብባልም ራራልኝ ጌ ነውሬን አልቆጠረም ፈሪሳዊያኑ አኝልበው ቢወስዱኝ ኢየሱስ ግን በፍቅር ፊት አየኝ በርኅራኄ@ አየኝ .. በፍቅር ፊት አየኝ በርኅራኄ@ አየኝ የተደበደበው አኝሌን ስላየ ስለእኔ መዋረድ አምላክ ተሰቃየ አወጣኝ ከድንጋይ ከቀያፋ በትር ለእኔ ያደረገውን ኸረ እንዴት ልዘርዝር /4/ ከዘማዊት ሴት ጋር አወራ ተብሎ መስቀል አደረገ ስሜን ተቀብሎ ቀራጭና ዘማን ያድናል ይባላል ትከሻው ሰፊ ነው እኛን ተሸክሟል /4/ ከኃጢአት ስወድቅ በሕይወት ዘመኔ ቸርነቱ በዝቷል በረከቱ ለእኔ መሐሪ መሆኑን ጌ ሲገልጽላት በልዩ ቸርነት ዘማዊቷን ጠራት /4/ ነውር ያለባችሁ ተሰብሰቡ በእርሱ ከውርደት ያድናል መሐሪ ነው እርሱ ለበሽተኞች ነው የመጣሁት ብሏል ነፍስና ቁስልህን ደዌህን የድናል /4/