የተወደደ ስምሽ ማርያም እንዳንቺ ንጹሕ በዓለም የለም አሳስቢልን እንዲምረን መድኃኔዓለም በንጽሕናሽ በመመረጥሽ ድንግል በእውነት እጹብ ድንቅ ነሽ አሳስቢልን እንዲምረን መድኃኔዓለም ፍጥረ ት አንቺን ይማጸኑሻል ከሲዖል ዓለም አውጪን ይሉሻል አሳስቢልን እንዲምረን መድኃኔዓለም አስራትሽን ኢትዮጵያን ጠቢቅልን ድንግል ሕዝቧን አሳስቢልን እንዲምረን መድኃኔዓለም