በዘር አንድ የሆነው ሌዋዊው ትቶኛል ባዕዱ ሳምራዊ ከሞት አድኖኛል በቁስሌ ላይ ዘይት የሚያስ ፍቅረኛ የሰላም ሰው ስጠኝ ሁነኛ ጓደኛ /2/ ከማይጠፋው ትውልድ ስለተወለድን አይቀርም እመኑ በምድር ዘራችን ከእግዚአብሔር ተወልደን ልጆች ተብለናል ባሮች አይደለንም ነጻነት ወጥተናል /2/ አንተን የሚመስል ቀናና የዋኅ ሰው ወንጌልኽን ነገረኝ ሕይወቴን ለወጠው ዓለም የሰጠችን ሞት ነበረ ድሮ ክርስቲያን አዳነኝ ወንጌልን አስተምሮ /2/ በሥጋና በደም የማልዛመደው በክርስቶስ ጥምቀት ዘሩ ከእኔ ጋር ነው ጓደኛዬ እርሱ ነው ሕይወት የሚሰጠኝ በቃሉ በፍቅሩ ተመስጫለሁኝ /2/ ልቡ ቅን የሆነ ጓደኛ መርጬ ሰላሜ ልዩ ነው ዛሬ ተለውጬ ክርስቲያን በሙሉ በዚህ ያስ ውቃል ፍቅሩ ይለውጣል ሥራው ይማርኝል/2/ ከዓለም ጉድጓድ ውስጥ መስዬ ወድቄ ይኸው ሰላም ሆንኩኝ ከአምላከ ርቄ እውነተኛ ፍቅር አስተማረኝና አዲስ አደረገኝ እኔን ክርስትና /2/