ተስፋ አለኝ በአምላኬ ተስፋ አለኝ በእግዚአብሔር ምናምንቴ ሆኜ በዚህች ምድር ብኖር ተስፋ አለኝ በእግዚአብሔር ጥበብ የተሞሉ ላላቅ ኃይለኞች ሥልጣን የጨበጡ የምድር ብርቱ−ች ስላልተመረጡ በሀብ ቸው ብዛት ተስፋ አለኝ ለጽድቁ ለሰማያዊ ቤት/2/ የአምላክ ዓይን ልዩ ነው አያዳላም ለሰው ፍቅሩ ለፍጥረቱ ምንጊዜም እኩል ነው ፀሐይን ለፍጥረት ያወጣል በእኩል ጻድቅና ኃጥእ ክፉ ሰው ነው ሳይል/2/ በኃጢአት ብወድቅም ሕይወቴ ቢገአድፍ በንስሓ ዳንኩኝ እኔ ሳልቀሰፍ አምላክ ቸርነቱ ምሕረቱ አድኖኝ አዲሲቷን ምድር እናፍቃለሁኝ /2/ ያለፈው በደሌ ተደምስሷልና ወደፊት ለፍቅሩ ለጽድቅ ሥራ ልቅና በዓለም ከሚኖሩ ባለተስፋ ሁነውሰላም ያገኛል ክርስቶስን መርጠው /2/