አልፈርድም እኔ በማንም በደል በማንም ኃጢያት በፈረድኩበት እንዳልመዘን ጌታ ሲመጣ በኃይል በሥልጣን በቸርነቱ አምላክ ባይተወው በደሌን ሁሉ ውስጤ ቢፈተሽ በተሰጠኝ ሕግ ለቅዱስ ቃሉ በምን ምግባሬ በሰው እፈርዳለሁ ዐይኔን አቅንቼ በደሌ በዝቶ ለራሴ ሳላውቅ በኃጢያት ሞቼ አልፈርድም እኔ አልፈርድም እኔ በማንም በደል በማንም ኃጢያት በፈረድኩበት እንዳልመዘን ጌታ ሲመጣ በኃይል በሥልጣን ይልቅ የአንዱን ሸክም ሌላው ሰው አዝሎ መጓዝ ይሻላል መፍረድ ከመጣ አንድም ሰው አይድን ሁሉም በድሏል ወንድም ወንድሙን እየከሰሰ ለፍርድ አቁሞ አሕዛብ ያያል ለንትርኩ እጅግ ተገርሞ አልፈርድም እኔ አልፈርድም እኔ በማንም በደል በማንም ኃጢያት በፈረድኩበት እንዳልመዘን ጌታ ሲመጣ በኃይል በሥልጣን ክርስቲያን ሆኖ ከወንድሙ ጋር እየተጣላ ዓለም ዳኘችን በፀብ ፍርድ ቤት ታረቁ ብላ ክርስቲያን ሆነን በአሕዛብ መሃል እየተካሰስን አምላክ አዘነ የመስቀሉን ፍቅር ዓላማ ስተን አልፈርድም እኔ አልፈርድም እኔ በማንም በደል በማንም ኃጢያት በፈረድኩበት እንዳልመዘን ጌታ ሲመጣ በኃይል በሥልጣን መቼ ከሰሰ የከሰሱትን የገረፉትን አይተናል እንጂ ለጠላቶቹ ምሕረት ሲለምን በጽድቅ ስራ ለእውነት ብለን መተናልእንጂ ማነው የሾመን በወንዲሞች ላይ አርጎ ፈራጅ