ነፍሴ ሆይ /2/ እግዚአብሔርን በቅን አገልግይ/2/ የተቀበለው በቀራንዮ ያን ሁሉ መከራ በመስቀሉ ላይ ለአንቺ ሲል ነውና ነፍሴ ሆይ ተዘጋጅተሽ ኑሪ ሁል ጊዜ በነገ በዛሬ እንዳት ለይ /2/ ነፍሴ ሆይ በንስሓ ጥምቀት ጠቢና ክቡር ደሙን ጠጪ ሥጋውንም ብይ /2/ ነፍሴ ሆይ ዘለዓለም በደስ እንድትኖሪ ከዘለዓለም ቤትሽ መንግሥተ ሰማይ መንግሥተ ሰማይ ነፍሴ ሆይ