መልእክተ ወንጌል በደሙ የጻፈ ስቃዩን ግሶ ችሎ ያሣለፈ በርሀብ በግርፋት በግካት አብዝቶ በገድል በትሩፋት ጠላትን ድል ነሰቶ ንዋየ ኅሩይ ነው ለዓለም ያበራ ሐዋርያው ጳውሎስ ለጽድቅ የተጠራ /2/ እንቅልፋን እያጣ ሌት ተቀን ሳይ ክት የኀእላውን ትቶ ተጓዘ ወደፊት በድኝም ተጠምዶ በገድል እያረሠ ከደማስቆ እስከ ሮም ቃሉን አዳረሠ እውነትን መናገር ከቶ ያላፈረ ሕዝብን ከአሕዛብ በአንድ ያስተባበረ አምላኩ እንዳይናቅ ከልቡ የተጋ ጸንቶ የተጓዘ ለምትበልጠው ጸጋ በሮም አደባባይ ሰማዕት የሆነ የተዋሕዶ አርበኛ ለአምላክ የ መነ በጣዕመ ስብከቱ ዓለሙን አጣፋጦ አክሊል ተቀዳጀ ሳይ ክት ሮጦ