አባታችን ሆይ የሁላችን ጌታ /2/ ቅዱስ መንፈስህን ስጠን በተርታሐ2ሐ ወደቷንተ መልሰዉ የሰዉን ልቦና /2/ ባላወቀዉ መንገድ እርሱ ሄዷልና እዝነ ምሕረትህን ወደኛ አዘንብል /2/ ይቅርታን ልንጠይቅ ከፊትህ ቆመናል ይቅርታን ልንጠይቅ ከፊትህ የቆምነዉ /2/ ምሐሪ መሆንክን ስለምናዉቅ ነዉ ትዕግሥትህ ሰፊ ነዉ አያልቅም ምሕረትህ /2/ የፍቅር ባለቤት ይቅር ባይ አንተ ነህ አይቶ እንዳላየ ታልፈዋለህ ሁለºን /2/ መዓቱም ምሕረቱም ሁሉም ያንተ ሲሆን ሥልጣንህ ረቂቅ ነዉ አይመረመርም /2/ ዘመንና ወራት ሊሽሩት አይችለºም የፍቅር ባቤት ቸሩ አምላካችን /2/ እድሜን ለንስሓ ስጠን ለሁላችንሐ2ሐ እንማልድሃለን በለቅሶ በሐዘን /2/ የይቅርታህ ብዛት ከእኛ ጋር እንዲሆን የሰማይ መላእክት የምድር ሠራዊት /2/ ያመሰግኑሃል በቀንና ሌሊት።