የሰዉ ልጅ ሁል ጊዜ በጣም ደስ ቢለዉ /2/ ደግሞ የጭንቁን ቀን ማሰብ ተገቢ ነዉ /2/ ምንም ቢደሰቱ ቢበዛ ምቾች /2/ ድኻም ሆነ ሀብታም እኩል ነዉ በሞት /2/ ሰዉ ሆይ አትጨነቅ ለዓለም ጐዳና /2/ ዓለሙም ንብረቱም ኃላፊ ነዉና /2/ ሀብት አገኘሁ ብለህ በጣም ደስ አይበልህ /2/ ድኸየሁም ብለህ አይዘን ልቦናህ /2/ ይፈራረቃለº አይኖሩም አብረዉህ /2/ %ረ ሰዉ ሆይ ልብህ ለምን ችላ አለ /2/ ከባድ የሞት እዳ በራስህ እያለ /2/ ያ የጨለማ ቀን ትዝ ትዝ እያለኝ /2/ እንባዬ ከመዉረድ አላቆምም አለኝ /2/