አቤት የዚያን ጊዜ ክርስቶስ ሲመጣ ትንሹም ትልቁም /፫/መድረሻውን ሲያጣ ከምሥራቅ ከምዕራብ ከሰሜን ከደቡብ አየራት ሲላኩ መላእክት ሲላኩ/፫/ መዓትን ለማዝነብ ሰማይና ምድር በአንድ ሲዋሃዱ የት ይሆን መድረሻው /፪/ የት ይሆን መንገዱ አቤት የዚያን ጊዜ ክርስቶስ ሲመጣ ትንሹም ትልቁም /፫/መድረሻውን ሲያጣ ጻድቃን በቀኝ በኩል ኃጥአን በግራ /፪/ ሲነፋ መለከት/፫/ ሲደለቅ እንዚራ ምድር ቀውጢ ስትሆን አጥንት ሲሰበሰብ/፪/ ኀፍረት ይይዘዋል/፫/ ሰው ለፍርድ ሲቀርብ አቤት የዚያን ጊዜ ክርስቶስ ሲመጣ ትንሹም ትልቁም /፫/መድረሻውን ሲያጣ ጩኸት ሲበረታ የማይጠቅም ለቅሶ/2/ እንደ ቁራ ጠቁሮ ጽልመትን ተላብሶ ገነትን ሲያገኙ ጻድቃን በሥራቸው ኃጥአን ወደ ሲዖል(፫) ተፈረደባቸው።