ጊዜዬ እስኪደርስ ወደአንተ መምጫዬ ለንሰሓ አብቃኝ አቤቱ ጌታዬ አቤቱ ጌታዬ ብርሃኔ መድኃኒቴ ተስፋህ ይመልሰኝ ጥፋቴን ደምስሰህ ይቅርታ አድርግልኝ ተስፋዬ እረዳቴ አንተ አትጣለኝ አምላኬ አታጥፋኝ ከሲኦል አድነኝ አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ መሐሪ ይቅር ባይ ምሕረትህ ይጎብኘኝ ከኃጢአት ፍላጻ ጸጋህ ይታደገኝ አዳኜ መድኃኒቴ ሰላምን ላክልኝ የድኅነት ደጆችህን በፍቅር ክፈትልኝ አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ አቤቱ ምሕረትህ በእኔ ላይ ይሁን ተጨነኩ ጌታዬ ስጠኝ ሰላምን ከክፉ እንድሸሽ አድነኝ እኔን በጎ እንድሠራ ምራኝ መንገዱን አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ሕይወት ሞት ድኅነት መኖራቸውን ባምንም ኃጢአት ውድቀት ጥፋት አያዘናጋኝም ሥርየት እንደማገኝ ተስፋ ቢኖረኝም ትምክህቴ አንተ ነህ በሌላ አልመካም አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ የበደሌ ብዛት የሚያስከፋም ቢሆን በሥጋ በደምህ እጠብ ኃጢአቴን ወዳንተ እመጣለሁ አደራ ነፍሴን በሰማያዊ ቤት አኑር ሕይወቴን አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥