ከእምነት አደባባይ አሻግሬ አይቼሽ እስካነጋግርሽ በዉኔ አግቃቼሽ አነጋግሪኝ ማርያም ጆሮዬ እንዲነቃ ኃጢአቴን እጠቢዉ አድርጊው ጥሩ እቃ ኦ! ድንግል ሆይ እጅግ ግሩም ነሽ የልቤ እንዲደርስ እንዴት ልበልሽ ኪሩቤል ሱራፌል አእላፍ መላዕክት ክብርት ናት አለº የጌታ እናት መልአክ የሚያጽናናሽ በቀኝም በግራ የሲና ሐመልማል የተቦር ተራራ አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ የልጅሽ ትሕትና ያንቺ ደግነት የክርስተያን ምርኩዝ የሆንሽ እመቤት እንዴት ላመስግንሽ የልቤ እንዲደርስ የትሕትና እናት የፍቅር ዉቅያኖስ አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ መዓዛሽ ያማረ ግሩም ጽጌረዳ እኔ አንቺን አምነኜ ፍጹም አልጎዳ ትሕትናን ልጫማ ፍቅርን ልልበስ ባንቺ አማላጅነት በመንፈስ ቅዱስ አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ %ረ እንዴነት ቢሆነዉ የምስተካከለዉ ዓይንሽን በዓይኖቼ እመቤት የማየዉ አንቺን የማይበት ምንም ዓይን የለኝ እንቅልፍ ሲወስደኝ በህልሜ ጥሪኝ አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ኃይልና ብርታቴ አንቺ ሁኝልኝ ከጠላት ስዋጋ ጋሻ ሆነሽኝ ማልቀስ አስተምሪኝ መሳቁ ይብቃኝ የሲዖል እሳቱ እንዳያቃጥለኝ አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ላስብሽ በአርምሞ ወደ ላይ መጥቄ /2/ የምድሩን ሳሳድድ እንዳልቀር ወድቄ /2/ አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥