የአብ ቃል አክብሮሽ እናት ያደረገሽ እግዚአብሔር በቃለ ፍጹም ያከበረሽ የምንመካብሽ መሰላል አንቺ ነሽ /2/ ቅድስና ላንቺ ጽድቅም ላንቺ ሆኖ ዓለምን የፈጠረ በአንቺ ተወስኖ የገነት ፍሬ ነሽ ሕይወትን ያፈራሽ አንቺን ለመረጠ አንቺን ላነጻሽ ምስጋና ይድረሰዉ ለቸሩ አምላክሽ /2/ አዳም የኖረብሽ የኤዶም ገነት ነሽ የኤፌሶን ወንዝ ወርቅ የሚፈልቅብሽ የግዮን ማዕበል ኢትዮጵያን የከበብሽ ዮርዳኖስን ሆነሽ አሕዛብን ፈወስሽ በልጁ ቃልነት አብም አከበረሽ /2/ መዓዛሽን ወዶ ወልድ ዋሕድ ዋጅሽ አብም በሰማያት በኅሊናዉ ሳፈሽ መንፈስቅዱስ መጥቶ አንቺን አከበረሽ እመካብሻለሁ እመቤቴ ስልሽ /2/ ወልድ በመዉደዱ ከአንቺ መወለዱን ንጹሕ ሆኖ አግኝቶት ቅዱሱ ሥጋሽን ለቃሉ ማደሪያዉ ጽላትና ታቦት በብሩህ ደመና ተመስለሽለት ከሥጋሽ ተከፍሎ ከደምሽ ደም ወስዶ ከነፍስሽም ነፍስ ፍጹም ተዋሕዶ /4/