ለዚህ ለኃጢአት ሕግ ከተሰጠ ከሕይወት መርገምን ከመረጠ ልሞት ከተሰጠ ከንቱ ኑሮ ማነዉ የሚያድነኝ ሞትን ሰብሮ ሥጋ በሥጋ ሕግ ይስበኛል መንፈስ በመንፈስ ሕግ ይጠራኛል ለየትኛዉ ጌታ ተገዝቼ የቱን እመርጣለሁ አንዱን ትቼ ኃጢአት እሰራና ይጨንቀኛል አምላኬ ሲለየኝ ይሰማኛል ጌታዬ ሲለየኝ ይሰማኛል አምላኬ ሲለየኝ ይሰማኛል አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ በኃጢአት በመኖር በዚህ ዓለም የአምላክን ትዕዛዝ በማጣመም በስርቆት በዝሙት በሰካር በዲያብሎስ ፈቃድ ስንኖር የኋላ የኋላ ዉድቀት ነዉ አምላክ በክንዶቹ ያልያዘዉ የጨለማ ጉዞ ምን ይጥማል ዓይን እያሳወረ ያዋርዳል አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ መላእክት በሰማይ ያለቅሳሉ የእግዚአብሔር ቅዱሳን ያነባሉ በኃጢአት ተማርከን ስንወሰድ ሰይጣን ድል አግኝቶ ስንዋረድ አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥