የሀብከ ዮም የሀብከ መድኃኔዓለም /2/ ዕድሜ ማቱሳላ ወአብርሃም /2/ ይስጣችሁ ዛሬ ይስጣችሁ መድኃኔዓለም /2/ ዕድሜ ማቱሳላ የአብርሃም/2/ በቅዱስ ጋብቻ ሙሽሮች የተወሰናችሁ /2/ ክርስቶስ ተገኝአል በመካከላችሁ /2/ የድንጋዮቹን ጋን ወይኑን ወይን ሊሞላበት /2/ ከድንግል ማርያም ጋር ተገኝአል ከዚህ ቤት /2/ ደስታዉን አይቶ አምላክም ፍጹም ተደስአል /2/ ሊባርካችሁም እጆቹን ዘርግአል /2/ በሕይወታችሁም ፍቅር ፍቅር ቅመም ሆኖ /2/ ትሕትናን ይሰጣችሁ እግዚአብሔር በቶሎ /2/ አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ሠርጋችሁ እንዲሆን ደስታ ፍቅር የተሞላበት /2/ በሕይወታችሁ ዉስጥ ክርስቶስ ይግባበት በሕይወታችሁ ዉስጥ አምላክ ይኑርበት አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ የበረከት ፍሬ በጸጋዉ እንዲበዛላችሁ /2/ ዛሬ& ተደሰቱ አምላክን ይዛችሁ /2/ እራስን በማገዛት ዕዉቀት /2/ ለመላችሁ /2/ ዛሬ ተደሰቱ አምላክን ይዛችሁ /2/ በሥጋ ወደሙ እግዚአብሔር ስለመረጣችሁ /2/ የመንፈስቅዱስም ሕፃናቶች ናችሁ /2/ አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥