ይእኛ ጌታ የኛ መድኅን በቸርነትህ ታደገን እኛ እንደሆን ኃይል የለን /2/ ጠዋት ለምልማ ታማ ጠፋች የሰዉ ኅሊና እያባባች ዓለም ምኗ ነዉ የጣፈጠን እያሳሳቀ የወሰደን አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ዛሬ አለሽ ሲሏት ትጠፋለች ከነተንኮሏ ዓለም ሟች ነች እሾህ በቅሎባት እሾህ ሆና በመተላለፍ ሰዉ ሊያልቅ ነዋ አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ከእኛ ጋር ያለዉ ኃይል ነዉ በሥጋዊዉ ዓይን ባናየዉ የጦሩ ብዛት መቼ ያድናል የዓለም ጥንስስ ተዋሕዷል አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ እንደሰዉ ጥበብ ጥበበኛ እንደሰዉ ወደር ወደረኛ እንደ ዓለም ጉልበት ጉልበተኛ በአምላክ ፊት ሲታይ ሕመምተኛ አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥