ብርሃን ወጣ ከመስቀሉ የሚያንጸባርቅ የአምላክና የሰው ልጆች እውነተኛ እርቅ ደስ ይበለን በመስቀሉ ብርሃን እልል እንበል በአንድነት ሆነን ድነት ሆነ ለመላው ዓለም ከፊት ለፊት በመሳሉ የመስቀሉ ነገር የሚወደው ሐዋርያ የወንጌል መምህር ዮሐንስም ስቅለቱን በማየቱ ሲያዝን ኖረ በምድራዊ ሕይወቱ ቢያሰቅቀው ሞቱ ግርፋቱ አዝ . . . ሞኝነት ነው ለሚጠፉት መሰናከያቸው በዓለም ጥበብ ለሚኖሩት እውነት ተስኗቸው ለጠቢብ ሰው በመንፈስ ለሚኖረው የመዳን ቀን እውነተኛ አርማ ነው ከገሃነም እሳት የሚያድን ነው አዝ . . . እስከ መስቀል ላልተለየው ቅዱስ ሐዋርያ ለዮሐንስ የወንጌል ሰው የፍቅር ባለሞያ ምስጋናችን ከምድር ይድረሰው እንድናለን በሰጠን ምሳሌው ሰ−ች ሁሉ እንከተለው አዝ . . .